የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አውጥቷል


ቢሮው በ5ኛው ዙርለጨረታ የቀረበው መሬት ፦ 
- በአራዳ
- በየካ
- በአቃቂ ቃሊቲ
- በአዲስ ከተማ
- በለሚ ኩራ
- በጉለሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎች እንደሆኑ ገልጿል።

በዚህ ዙር 427 የሚሆኑ ቦታዎች ለጨረታ መቅረባቸው ተጠቁሟል።

በተለይ አቃቂ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች በርካታ ስፋት ያላቸው ቦታዎች መቅረባቸው ነው የተነገረው።

በ5ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2 ሺህ 300 ብር በቴሌብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ/ም ቀን 9 ሰዓት ድረስ ከ 2merkato.com / https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link-https: addisland.afrotender.com) ላይ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ተጫራቾች ቦታዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባቸው ተብሏል።

አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት እንደማይችል ተገልጿል። ተጫርቶ ቢገኝ ግን ከጨረታው ውጭ እንደሚሆን ተመላክቷል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ 50 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ለየቦታ ኮዱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ከ50 በመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ እንደማይችልም ተገልጿል።

ሌላው ከአዲስ አበባ ውጭ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ሲሰራ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች ጋር በኔትዎርክ የተያያዘ መሆን ያለበት ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር " እኔ አልጠየቅም " ብሏል ቢሮው።



አስተያየቶች

ታዋቂ ልጥፎች